ከአጋርነት፡ ወደ ሃገር ባለ ቤትነት፡ ፕረዚደንት ሙስጠፌ

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለሚተላለፉ የሐሰትመረጃዎች
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ የሐሰት መረጃዎች የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር ሙስጠፋ ሙሐመድ ኦመር ሆነ ተብሎ በተቀነባበረ ድምፅ ቅጅ ያልተባለ ንግግር አደረጉ ተብሎ እየተነገረ ነው፦
“ዶ/ር አቢይ አህመድ ከስልጣኔ ቢያነሱኝ ክልሉ ይፈርሳል፣ ኢትዮጵያም አትቆይም።” የሚለው አርእስት የአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ወኪሎቹ የተጠቁመበት አርእስት ነው
ይህ መረጃ ግልጽ የሐሰት ፈጠራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ፈፅሞ ያልተናገሩት ነው፡፡
ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙ እውነታዎች እንደሚከተሉት ናቸው፦

  1. ስለተሰራጨው ድምፅ
    አንዳንድ ተቆራርጠውና ተቀጣጥለው የሚለቀቁ ነገሮችን ሁሉ ተከታትለን መልስ ብንሰጥ ስራ የምንሰራበት ግዜ አይኖርም፡፡
    ነገር ግን ይህ አይነት ነገር ትላንት ሀገር እያፈረሱ ፣ ሀገር አፍራሽ ሲሉን የነበሩ፣ ህዝባችንን ሲጨፈጭፉና ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር ቆመው ዜጎቻችን ላይ ግፍ ሲፈፅሙ የነበሩ ከጀርባ የሚዘውሩት መሆኑን እናውቃለን፡፡
    መጪው ምርጫ እንደመሆኑ በቀጣይነትም ይህ ዘመቻና ካራክተር አሳስኔሽን በተለያየ መንገድ እንደሚቀጥልም እናቃለን፡፡
    ይህንን ህዝብ ከኢትዮጵያዊነቱ ሊነጥሉት ሲሞክሩ የነበሩ አካላት ዛሬ ሀገር ሊያፈርሱ ነው ሲሉ አንደመስማት አስገራሚ ነገር የለም፡፡
    ሀገር ለመበተን ወያኔ ሀገር ሲወር እኮ ይህ ህዝብ ነው ከመከላከያ ድንበር ተርክቦ ሲጠብቅ የነበረው፣ደም ያፈሰሰው፣ ከአልሸባብ ጋር ተናንቆ ሀገር ያቆመው! ታዲያ ማነው ሀገር አፍራሹ ማነውስ ሀገር ገንቢው? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
  2. ወጣ በሚል ስለሚሰራቸው የተቀጣጠለ ደምፅ ደግሞ
    ቃለ-መጠይቁ የተሰጠው በዚያን ጊዜ በነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ምክንያት ሲሆን፣
  • ONLF በክልሉ ውስጥ መንግስቱ በፌዴራል ትእዛዝብቻ መጣ የሚል የሐሰት ወሬ እየሰራጨ ነበር
  • ህዝቡ በክልሉ መንግስት ላይ እንዲነሳ እና እንዲያመፅ የሚያነሳሱ ሀይሎች ነበሩ
  • የሰሜኑ ጦርነት ሁኔታ የክልሉን ሰላምና መረጋጋት እየነካውም ነበር
    ስለዚህ ህዝቡን ለማረጋጋት፣ እውነቱን ለመግለጽ እናየሐሰት መረጃን ለመከላከል ቃለ-መጠይቁ ተሰጠ።
  1. በቃለ-መጠይቁ ውስጥ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚል ንግግር የለም
    ቃለ-መጠይቁ ውስጥ ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን ቢነሱ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ወይም ክልሉ ከአገሪቷ መእቀፍ ይለያል የሚል ንግግር አልተነገረም።
    ይህ ንግግር ከቃለ-መጠይቁ ተቆርጦ በኋላ የተፈጠረ ሲሆን ህዝብን ለማወናበበድ እና ገፅታ ለማበላሸት ታስቦ ነው የተሰራጨው
    የዚህ ዓይነት ወሬ ዓላማ ጥርጣሬ መፍጠር፣ ህዝብን መከፋፈል እና ውዥንብር ማስነሳት ነው።
  2. ሌሎች የሚሰራጩ የሐሰት መረጃዎች
    በዚህ የተቆራረጠ ድምፅ ተራ የሴራ ንድፈ ሀሳብ (Conspiracy Theory) ለመስራት ተሞክሯል…
    አንዳንዶች ቃለ-መጠይቁ ቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በክልላችን ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ሲመርቁ አደረጉት ለተባለው ንግግር የተሰጠ መልስ ነው ይላሉ፤ ይህ ግን ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡
    ሲጀመር ጠቅላይ ሚንስትሩ በሶማሊ ክልል ግዙፍ ፕሮጀክት ሲመርቁ የክልሉ አስተዳደር እና ካቢኔ በልማትም ሆነ በሰላም ዘርፍ እጅግ ግዙፍ ስኬት እንዳሰመዘገቡ በመመስከር እውቅና ሰጥተዋቸዋል።
    “2 ፐርሰንቱ ነው የተነካው” የሚለው አገላለለፅ ሶማሊ ክልል ካለው ፀጋ አንፃር ገና ብዙ አልነካነውም ከሚል እይታ የተሰጠ ነው። የክልሉ መንግስትም በዚህ መንገድ ነው የተረዳው።
  • የአቶ ሙስጠፌ ቃለ-መጠይቅ በፈረንጆቹ 2021 ነወ የተሰጠው
  • ጠቅላይ ሚንስትሩ ይሄንን ንግግር ያደረጉት ደግሞ በ2026 ነው
    ስለዚህ 2021 የተሰጠ ንግግር 2026 ለተነገረ ነገር መልስ መሆን አይችልም – ሊሰራ የታሰበው የሴራ ንድፈ ሀሳብ (Conspiracy Theory) ከሸፈ ማለት ነው።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩም ስለ ክልሉ ሲናገሩ
  • ከመጀመሪያ ምስጋና እና አድናቆት አቀረቡ
  • ከለውጡ በኋላ ታላቅ እድገት ተመዝግቧል አሉ
  • አመራሩ ታማኝነት እና ጥረት አሳይቷል አሉ
  • አሁንም ተጨማሪ ሥራ ያስፈልጋል አሉ
    ይህ ንግግር ለማበረታታት ነው እንጂ ለመነቃቀፍአይደለም።
  1. የሶማሊ ክልል እና የፌዴራል መንግስት ድጋፍ
    የሶማሊ ክልል ከዶ/ር አቢይ አህመድ መሪነት በኋላ በብዙ ዘርፎች እድገት አሳይቷል፦ እንዲያውም በኢትዮጵያ የተረጋጉ ከሚባሉት አካባቢዎች መካከል ቀዳሚው ነው…
  • የፖለቲካ መረጋጋት
  • የኢኮኖሚ እድገት
  • መሰረተ ልማት
  • ትምህርት እና ጤና
  • የስራ እድል መስኮች ከሚቀሱት መካከል ይገኙበታል…
    ስለዚህ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ በድጋሚ እናረጋግጣለን፦
  • የሶማሊ ክልል መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር አንድ ነው
    እንዲያውም በኢህአዴግ አገዛዝ ከነበረን የአጋርነት ደረጃ ህዝባችን ወደ ሀገሪቱ እውነተኛ የስልጣን ባለቤትነት የተሸጋገረበት ስርአት ነው – አሁን ያለው መንግስት…
  • የኢትዮጵያን አንድነት ይጠብቃል
  • ልዩነት የሚባል ፈፅሞ የለም
  1. መደምደሚያ
    የሐሰት መረጃ ስርጭት ዓላማው
    ህዝብን ለማጋጨት
    ህዝብን መከፋፈል
    የህዝብን አንድነት ለማዳከም ነው።
    በህዝብ እና መንግስት መካከል ክፍተት ለመፍጠር- ወ.ዘ.ተ
    ስለዚህ ህዝቡ ከነዚህ ነገሮች ሊጠነቀቅ ይገባል፦
  • ያልተረጋገጠ መረጃ አለማመን
  • ኦፊሴላዊ መረጃ ብቻ መከታተል
    ይህን መሰል መርዘኛ መረጃ ከተገቢው አካል ማጣራት
  • አንድነትቹህን ጠብቁ

* ሰላምን ማስጠብቅ የጋራ ስራችን መሆኑን ማወቅ

የክልሉ መንግስት ሁልጊዜ የቆመው:
ለአንድነት — ለሰላም — ለልማት — ለአገር አንድነት ነው፡፡
 
 

#ማሳሰብያ፡ይህ የሶማሌ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የላከልን ዘገባ ሲሆን የሚድያችን አቋም አለመሆኑን ከወዲሁ ልንገልፅ እንፈልጋለን። መዘገብና ማሰራጨትም የሃሳቡ ባለ ቤትነት አለመሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *